Tuesday, August 5, 2014

የሕወሓት ጄኔራሎች ሲታመሱ ዋሉ ። በሰራዊቱ ውስጥ አለመተማመን ነግሷል።

ምንሊክ ሳልሳዊ


በጥርጣሬ/ግምት ካልሆነ በቀር አስራ አራቱ መኮንኖች የት እንደገቡ አይታወቅም።
ሁለት ከፍተና የጦር መሃንዲስች ዱካቸው ደብረዘይት ከሚገኘው እስር ቤት ተገኝቷል።
ወደ መቀሌ ከዲያስፖራው ጋር ለዘረፋ የንግድ ሽርክና ኢንቨስተሮች ለመመልመል ያመሩት ጄኔራሎች ሳይቀሩ በምን እንደመጡ በማይታወቅበት ሁኔታ አዲስ አበባ ደርሰው የመሃል አገር መኮንኖች መጥፋትን ተከትሎ ያመጣውን ውጥረት በስብሰባ ሲያሹት እና ከተለያዩ ወታደራዊ ደህንነቶች መረጃ ሲሰበስቡ እንደዋሉ ታውቋል።

በሰራዊቱ ውስጥ አለመተማመን የተፈጠረው ከምን የመነጨ ነው የሚል ጥናት በዚህ ሳምንት በተካሄደበት የመሃል አገር መከላከያ መምሪያዎች ውስጥ አጋጣሚ በተገኘ መረጃ 16 ከፍተኛ የጦር መኮንኖች የት እንደገቡ አይታወቅም ሲል ሪፖርት ያቀረበው የወታ
ደራዊ ደህንነት ቡድን የቀረበለትን ጥቆማ ለበላይ አካላት ሪፖርት ሳያድርግ ፍተሻውን አጧጡፎት የነበረ ቢሆንም ምንም አይነት 
ፍንጭ ባለማግኘቱ ትላንትና የተነገረው የበላይ አካል በከፍተኛ ድንጋጤ ተውጦ የዋለ መሆኑን ለጦር ክፍሎቹ ቅርብ የሆኑ ምንጮ
ቻችን ከመከላከያ ያደረሱን መረጃ ጠቁሟል።

ከመሃል አገር በተለያየ የጦር መምሪያ ውስጥ ተመድበው ይሰሩ የነበሩት እና የአንድ ኮርስ ምሩቅ ናቸው የተባሉት ወታደራዊ መኮ
ንኖች ውስጥ የሕወሓት ጄኔራሎች ላይ ጥርሱን እንደነከሰ የሚነገርለት ኮሎኔል አለም የሚባለውን የተንቤን ተውላጅ ጨምሮ አስረ
 አንዱ ወደ ደቡብ ሱዳን ዘልቀው ገብተዋል የሚል መረጃዎች ቢኖሩም እስካሁን ማረጋገጥ እንዳልቻለ ለመከላከያ ደህንነት ቢሮ ምንጮቻችን የገለጹ ሲሆን የሶስቱ ዱካ አለመገኘቱን እና ሁለት ከፍተኛ የጦር መሃንዲሶች ከየት ታፍነው በማን ታፍነው እንደተወሰዱ ሳይታወቅ በደብረዘይት የምድር ውስጥ እስር ቤት እንደሚገኙ ተረጋግጧል።

የሕወሓት ጄኔራሎችን ያመሳቸው ጉዳይ የተንቤን ተወላጆች ሌሎች የደቡብ እና የአማራ ተወላጆች ተያይዞ መጥፋት ሲሆን
 እንዲሁም በጦር ሰራዊቱ ውስጥ እየላላ መጥቷል ሲሉ የደነፉበት የወታደራዊ ደህንነት ቁጥጥር መላላት ለነገው የስልጣን እድ
ሜያቸው ከፍተኛ ስጋት እንዳጠላበታ ያሳያል ሲሉ መረጃውን የላኩልን የመከላከያ ምንጮቻችን ተናግረዋል። በሙሉ የሃገሪት
 እዞች ከፍተኛ ቁጥጥር እና ፍተሻ እንዲካሄድ በዛሬው ስብሰባ ጥብቅ ትእዛዝ ያስተላለፉት የሕወሓት ጄኔራሎች በደቡብ እና 
በምእራብ ድንበሮች አከባቢ ያሉ እንቅስቃሴዎች እንዲፈተሹ በወጪ ገቢው ላይ ከፍተኛ ቁጥጥር እንዲደረግ እና የየቀኑ ሪፖርት 
እንዲላክ እንዲሁም በመሃል አገር ያሉ የቶር መኮንኖች በየቀኑ ለቅርብ አለቃቸው ዝርዝር የአባላት እንቅስቃሴ ሪፖርት እንዲያቀርቡ
 ጥብቅ ትእዛዝ አውርደዋል።እንዲሁም ተጨማሪ ወታደራዊ ደህንነቶች በየእዙ እንዲመደቡ አዘዋል።

በዚህ ዙሪያ ያለውን ጉዳይ በተመለከተ የወታደራዊ ደህንነት ሪፖርቶቹን እየተከታተልን የምናቀርብ መሆኑን ቃል እንገባለን።

No comments:

Post a Comment