Wednesday, August 6, 2014

የአርባ ምንጭ ከተማ የሰማያዊ ፓርቲ መሪዎች ታሰሩ

ሐምሌ ፴(ሠላሳ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የዞኑ ፖሊሶች ትናንት ከሌሊቱ 10 ሰአት ላይ ወደ ሰማያዊ ፓርቲ የአርባ ምንጭ አመራሮች መኖሪያ ቤት በመሄድ ፍተሻ ካደረጉ በሁዋላ ፣ አመራሮችን ወስደው አስረዋቸዋል።

የፍርድ ቤት ማዘዣ ይዘናል በማለት ፍተሻ ያካሄዱት ፖሊሶች በአንደኛው ቤት ውስጥ ሁለት ፍሬ ጥይቶችን ማግኘታቸውን ሲያስታወቁ፣ በሌሎች መኖሪያ ቤቶች ደግሞ
ቪዲዮ ካሜራዎችን፣ ፊልሞችንና የተለያዩ ወረቀቶችን ሰብስበው ወስደዋል። የአንደኛው አመራር የቅርብ ሰው የሆነ ለኢሳት ሲናገር፣ ፖሊሶቹ ጠመንጃ በሌለበት ሁለት
ጥይቶችን አገኘን ማለታቸው አስቂኝ ነው ካለ በሁዋላ፣ ሁለቱንም ጥይቶች ፖሊሶች ራሳቸው ይዘው መምጣታቸውንና አገኘን ብለው መናገራቸውን ገልጿል።

ሉሉ መሰለ፣ በፈቃዱ አበበ፣ ነጻነት መተኪያና ኢ/ር ጌታሁን በየነ የተባሉት አመራሮች ገሚሶቹ በአርባ ምንጭ ከተማ ቀሪዎቹ ደግሞ ከከተማው ወጣ ብሎ በሚገኝ እስር ቤት መታሰራቸው ታውቋል። ኢህአዴግ መራሹ መንግስት የሰማያዊ ፓርቲ የምክር ቤት ምክትል ሰብሳቢ የሆነውን አቶ የሽዋስ አሰፋን እንዲሁም የፓርቲው አባል የሆነቸውን ወይንሸት ሞላን በቅርቡ ማሰሩ ይታወሳል።
መንግስት በሽብር ሰበብ ካለፉት ሁለት ወራት ጀምሮ በብዙ መቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ይዞ አስሯል። አንዳንድ ወገኖች የአሁኑን እስር ከመጪው ምርጫ
ጋር እያያዙት ሲሆን፣ ሌሎች ደግሞ
በአገሪቱ ውስጥ የሚታየው የኑሮ ውድነትና የፍትህ እጦት በህዝቡ ዘንድ የፈጠረውን  ስሜት ተቃዋሚዎች እንዳይጠቀሙበት አስቀድሞ የመከላከል እርምጃ እየተወሰደ ነው ይላሉ። በሌላ ዜና ደግሞ ዋስትና የተፈቀደላቸው ሙስሊም ፖሊሶችና የሰማያዊ ፓርቲ አባሏ ወ/ት ወይንሸት ሞላ እንደገና እንዲታሰሩ ተደርጓል።
ሪፖርተር እንደዘገበው በአንዋርመስጊድውስጥ በቅርቡ ተፈጥሮ የነበረውን ግጭት አስተባብረዋል ተብለው የታሰሩ ሙስሊምየፖሊስአባላት ፣ የታሰሩት የአድማ በታኝ ፖሊስ አባላት መሆናቸውን መታወቂያ በማሳየታቸው ብቻ መሆኑን ለፍርድ ቤት ተናግረዋል።
ሐምሌ 29 ቀን 2006 ዓ.ም. በአዲስአበባከተማየመጀመሪያደረጃፍርድቤትየጊዜቀጠሮማስቻያችሎትለአራተኛጊዜበቀረቡበት ወቅት በግጭቱአለመሳተፋቸውን ተናግረዋል። ኮንስታብልአብዱራህማን  ወንድሙንለመጠየቅበመሂደበት ጊዜ፣የፀሎት ሰዓት ስለደረሰበት አንዋርመስጊድ ሰግዶ በመመለስ ላይ እንዳለ መያዙን ገልጿል።
ኢንስፔክተር  መሐመድ የሱፍ ደግሞ በመስጊድ ውስጥ እየሰገደ  በነበረበት  ወቅት ግጭቱ በመነሳቱ እዚያው መቆየቱንና መታወቂያውን ለአንድ የፖሊስ አባል ሲያሳይ ‹‹ውስጥ ለምን ገባህ? ፖሊስ ሆነህ እንዴት እዚህ ልትገባቻልክ?›› ተብሎ መያዙን ገልጿል።
ኢንስፔክተር ሙሃመድ  እሱበመስጊድውስጥባለበት ጊዜ ከውጭብጥብጥመነሳቱን ገልጾ፣ እንኳንስ ለክስ ይቅርና ለምስክርነት እንደማይበቃ ገልጿል፡፡“ፖሊስሆኖበመስጊድውስጥወይምአካባቢመገኘትየማይቻልከሆነ፣ይህንንእንደትምህርትእንደሚወስደውበመናገርበዋስከእስርተለቆ፣ወደፊት
የሚጠየቅበትጉዳይካለሥራውንእየሠራ
እንዲጠባበቅፍርድቤቱን” መጠየቁን ጋዜጣው ዘግቧል።
ሌላው እስረኛ ምክትልኢንስፔክተርአደምመስጊድውስጥእንደነበረና  ብጥብጡካበቃበኋላከቀኑአሥርሰዓትላይመያዙን ገልጾ፣  ፖሊስ በመሆኑ ብቻ መያዙንእንዲሁም ከተያዝኩበትቦታ
እስከ ጣቢያ ድረስ እየተደበደበ መወሰዱን ” ተናግሯል፡፡ለ19 ቀናትመታሰሩን፣  ቤቱ ሲፈተሽ ምንም ነገር አለመገኘቱን፣  ሙስሊም በመሆኑ ብቻ መጠየቅ እንደሌለበት አስረድቷል።
ከዚህ ቀደም  የፀጥታ (ኢንተለጀንስ) ሥራስትስራ እንደነበርናተገቢያልሆነባህሪ በማሳየቷ ቢሮውስጥእንድትሠራመደረጓንበመርማሪፖሊሶችለፍርድቤት
የተነገረላትምክትልሳጅንሳሊናመሐመድ
፣ፖሊስ ለምርምራ በሚል የሚወስደውን የጊዜ ቀጠሮ ተቃውማለች።
እንደ ጋዜጣው ዘገባ ሳጅን ሳሊና “መርማሪፖሊስመረጃለመሰብሰብከበቂበላይጊዜመውሰዱንናየፌዴራልፖሊስበብጥብጡዕለትየቀረፀውን
የቪዲዮማስረጃእንዲሰጠውበደብዳቤ  ጠይቆእየተጠባበቀ መሆኑንለፍርድቤትያስረዳውተገቢአለመሆኑን”ተናግራለች።
” እሷየኦዲዮቪዥዋልክፍልሠራተኛእንደነበረችበማስረዳትፖሊስለማስረጃየሚፈልገውምሥልመኖሩንበደብዳቤሲገልጽበአሥርደቂቃውስጥማግኘት
እንደሚቻልአስረድታለች፡፡ቤቷን፣ተንቀሳቃሽስልኳንናየሚፈልጉትንነገርሁሉመርምረውናፈትሸውምንምያገኙባትነገርእንደሌለአስረድታ፣የተሰጠውቀንከበቂ
በላይመሆኑንበመጠቆምተጨማሪጊዜሊፈቀድ እንደማይገባተቃውማለች፡፡”
ፖሊስ ከፍርድ ቤት ለቀረበለት ጥያቄ ፣” ፖሊስ 12 ተጠርጣሪዎችበዕለቱበሰዎችላይጉዳትማድረሳቸውን፣ንብረትማውደማቸውን፣የደበደቧቸውፖሊሶችና
ሰላማዊሰዎችበተለይበሆስፒታል ኮማውስጥያሉትመናገርእንደማይችሉበማስረዳት፣
የተጎዱትሰዎችባይድኑተጠርጣሪዎቹዋስትናበሚከለክለውየሰውመግደልወንጀልተጠርጥረውስለሚከሰሱዋስትናእንዳይፈቀድላቸው” ጠይቋል።
የሰማያዊፓርቲአባልየሆነችውወ/ትወይንሸትሞላ፣እምነቷበማይፈቅድላትቦታበብጥብጡውስጥመገኘቷንናብጥብጡንስታበረታታናየተለያዩመፈክሮችንየያዙበራሪ
ወረቀቶችንስትበትንእንደነበርፖሊስ ገልጿል፡፡
የአዲስጉዳይመጽሔትፎቶጋዜጠኛአዚዛመሐመድእምነቷእስልምናቢሆንም፣በሁከቱቦታተገኝታስትመራናስታግዝነበር ሲል መርማሪ ፖሊስ ለፍርድ ቤቱ ተናግሯል።
የሰማያዊፓርቲአባሏወ/ትወይንሸትመርማሪዎቹየወሰዱትየምርመራጊዜበቂመሆኑንተናግራለች፡፡ ወይንሸት በፖሊስ የቀረበውን ውንጀላ አስተባብላለች።
ጋዜጠኛ አዚዛ መሐመድም ወደ ሥፍራው የሄደችው ሥራዋን ለመሥራት ብቻ መሆኑን ተናግራለች። ፍርድ ቤት በመጨረሻም ተጠርጣሪሙስታዝመንሱር፣  የሰማያዊፓርቲአባልወ/ትወይንሸትሞላናየአዲስጉዳይመጽሔትፎቶጋዜጠኛአዚዛመሐመድእያንዳንዳቸው
በአምስትሺሕብርዋስእንዲለቀቁበማዘዝ፣ በሌሎቹተጠርጣሪዎችላይየስምንትቀናትጊዜበመፍቀድ ለነሐሴ 7 ቀን 2006 ዓ.ም. ተለዋጭቀጠሮሰጥቷል፡፡
ሦስቱተጠርጣሪዎችበአምስትሺሕብርዋስእንዲፈቱፍርድቤቱቢወስንም፣  መርማሪፖሊስበሰዓታትልዩነትለአዲስአበባከተማነክሰበርሰሚችሎት
ይግባኝአቅርቦ፣ ‹‹ይፈቱ›› የሚለውንውሳኔበማሻርበሦስቱምተጠርጣሪዎችላይተጨማሪየሰባትቀናትየምርመራጊዜጠይቆ ተፈቅዶለታል።

No comments:

Post a Comment