Thursday, July 17, 2014

በአውሮፓ በድምጻዊ ማዲንጎ አፈወርቅ ላይ ቦይኮት ተጠራ

madingo
በሕወሓት አስተዳደር ስር የሚመራው ሜጋ አምፊ ትያትር ስር በአባልነት ሲያገለግል የቆየውና በጀርመን ሃገር ለ12ኛ ጊዜ በሚደረገው የስፖርት ዝግጅት ላይ የሙዚቃ ሥራዎቹን ለማቀረብ የሚያቀናው ማዲንጎ አፈወርቅ ከፍተኛ የሕዝብ ተቃውሞ ገጠመው፤የሙዚቃ ኮንሰርቱ እንዳይደረግ ከፍተኛ ጥረት እናደርገጋለን ብለዋል።

በተለይ ከገዢው ፓርቲ ጋር ለመስራት ፍላጎት የሌላቸውን አርቲስቶች ለመንግስት ሃይሎች በመሰለል ይታወቃል የተባለው

በሕወሓት አስተዳደር ስር የሚመራው ሜጋ አምፊ ትያትር ስር በአባልነት ሲያገለግል የቆየውና በጀርመን ሃገር ለ12ኛ ጊዜ በሚደረገው የስፖርት ዝግጅት ላይ የሙዚቃ ሥራዎቹን ለማቀረብ የሚያቀናው ማዲንጎ አፈወርቅ ከፍተኛ የሕዝብ ተቃውሞ ገጠመው፤ የሙዚቃ ኮንሰርቱ እንዳይደረግ ከፍተኛ ጥረት እናደርገጋለን ብለዋል።

ማዲንጎ በተለይ በቅርቡ አማሮች ከደቡብ ክልል ሲባረሩ የመንግስት እርምጃ ትክክል ነው በሚል በግልጽ ተናግሯል በሚል ማህበራዊ ድረገጾች ወቀሳ ሲሰነዘርበት እንደነበር የቅርብ ጊዜ ትዝታ ነው።
በአላሙዲ/ወያኔ ኮንሰርቶች ጋር በመሳተፍ ብዙሃኑን የኢትዮጵያ ሕዝብ አስቀይሟል፤ የወያኔ ሰላይ ነው፤ በሚል ተቃውሞ የገጠመው ማዲንጎ የፊታችን ኦገስት መጀመሪያ በጀርመን የሙዚቃ ኮንሰርት እንደሚያቀርብ ከተሰማ ወዲህ በዛው አካባቢ የሚገኙ
 በአርቲስቱ ስም ላይ ቀይ መስመር በማስመርና የወያኔን ባንዲራ በማልበስ ሕዝብ እርሱ በሚገኝባቸው ኮንሰርቶች ላይ እንዳይታደም ጥሪ ተደርጓል።
በዚህ ዙሪያ ዘ-ሐበሻ ድምጻዊ ማዲንጎ አፈወርቅን ለማነጋገር ያደረገችው ጥረት አልተሳካም።

No comments:

Post a Comment