Thursday, November 21, 2013

የህወሓት እኩይ ተግባር እያደረ ይገለጣል!!

 (ኢንጂኔር አብደልውሀብ ቡሽራ - መቀሌ)
ከሁለት ሳምንታት በፊት ወደ ሽሬ ለመሄድ ወደ መቀሌ አውቶብስ ተራ ሄድኩና በሰላም ባስ አውቶብስ ተሳፍሬ ጉዞየን ጀመርኩ:: እየተጓዝን እያለን በተቀመጥኩበት ወንበር አጠገብ ሁለት ሰዎች ነበሩ:: ሰዎቹ ከዛ በፊት አይቻቸው አላውቅም:: ሁለቱም አካል ጉዳተኞች ናቸው:: በመንገዳችን እየተጓዝን እያለን ሁለቱ ሰዎች የድሮ ትዝታቸው እያነሱ እያወሩ ነበሩና እኔም የነሱ ወሬ አዳምጥ ነበርኩ:: እንደዛ ቆየሁና ወሬያቸው ታሪካዊና የድሮ ትዝታቸው ስለጣመኝ በመሃላቸው ገባሁና ተዋወቅኩዋቸው:: እነዛ ሰዎች ሁለቱም የቀድሞ
የህወሓት ታጋዮች የነበሩና በትግሉ ጊዜ አካላቸው የተጎዱ መሆናቸው አወቅኩ:: እንደዚህ እያወራንና
እየተጨዋወትን ረጂም ጊዜ አለፈ:: በጨወታችን ማሀል አንዳንድ ጥያቄዎች አቀርብላቸው ነበር:: እነሱም
ለምጠይቀውን መልስ ይሰጡኝ ነበር:: በመቀሌ ከተማ ፍረስወአት የሚባል የእንጨትና የብረት ሥራዎች
የሚሰራና ሥራው በአካለ ጉዳተኞች የሚካሄድ ድርጅት አለ:: ከአስር ዓመት አካባቢ በፊት በድርጅቱ ብዙ ረብሻዎች የሥራ ማቆም አድማና ሰላበማዊ ሰልፍ ለማድረግ ሙከራ እንደአደረጉና በፀጥታ ኃይሎች እንደታገዱ አውቅ ነበር:: በዛን ጊዜ ያን ችግር በሚመለከት ብዙ ጊዜ በጋዜጦች ፅፌ ነበር:: የችግሩ መነሻ የሆነው በድርጅቱ ብልሹ አስተዳደርና በሰራተኞች መካከል የነበረ የአሰራር ብልሹነት ችግር ምክኒያት ነው:: ምክኒያቱም የአስተዳደር ሥራ በአካለ ጉዳተኞች ያልሆኑ ሰዎች ይካሄድ ስለነበረና እነሱ ደግሞ የሚፈጥሩት ችግር ነው:: ይህን ሁሉ እያነሳን ብዙ አወራን ሃሳብ ለሃሳብ ተለዋወጥን::

Tuesday, November 12, 2013

”ኢትዮጵያዊ መልኩን ነብር ዥንጉርጉርነቱን ሊቀይር ከቶ ይቻለዋልን?”





ኢትዮጵያዊ መልኩን ነብር

ዥንጉርጉርነቱን ሊቀይር
ከቶ ይቻለዋልን?”
(ትንቢተ ኤርምያስ 13:23)

                                                                                                                                     
 -ከምናሴ መስፍን - ኖርዌይ
በዚች ባለንበት ፕላኔት ላይ የሰው ልጅን አስተሳሰብ ወይም ህገ ልቦና ከሚዳኙት ረቂቅ ክንውኖች መሀከል የስነ መለኮት ወይም የስነ ፅሁፍ ሀብቶች ውስጥ ታላቁ መጽሐፍ (መጽሐፍ ቅዱስ) አቢዩ ነው። ታላቁ  ይናገራል።
ምንም እንኩዋን በአገራችን የኢትዮጵያን ታሪካዊ ጠላቶች ዘመቻ - ከውጭም ሆነ ከውስጥ እኩይ ጡት ነካሽ ልጆችዋም የሚሰነዘሩ፤ ዘርፈ ብዙ እርሷነትዋን የማጥፋት ዘመቻዎች እጅግ ይበዛሉ፡፡ ያም ሆኖ እነርሱ እራሳቸው እንቅልፍ ያጣሉ እንጅ አምላክ በቃል ኪዳኑ ስለሚጠብቃት አንዳች አትሆንም።