Tuesday, April 30, 2013

“የተዘነጉት እስረኞች” እና የተዘነጋው የቤተሰቦቻቸው ስቃይ





ላለፉት አራት ዓመታት ቃሊቲ ማረሚያ ቤት ቅዳሜ እና እሁድ የሄደ ሰው ወጣቷን ናርዶስን ሳያገኝ አይመለስም፡፡ ናርዶስ ገና የ20 ዓመት ወጣትእና በኪያሜድ የመጀመሪያ ዓመት የነርሲንግ ተማሪ ናት፡፡ ናርዶስ ዘሪሁን በየሳምንቱ ቃሊቲ ማረሚያ ቤት የምትመላለሰው በ‹‹አሸባሪነት›› ‹በእነብርጋዴር ጄኔራል ተፈራ ማሞ መዝገብ› ከተከሰሱት 36 ሰዎች መካከል ዕድሜ ልክ የተፈረደባትን እናቷን ልትጎበኝ ነው፡፡ እነዚህ እስረኞች ሚያዝያ 16/2001 አመሻሹ 12 ሰዓት አካባቢ ነበር ሁሉም በያሉበት በቁጥጥር ስር የዋሉት፡፡ እኛም 4ኛ ዓመታቸውን ለማሰብ ተሰባስበን ወደቃሊቲ ማረሚያ ቤት በተለይ እማዋይሽ ዓለሙን ለመጠየቅ ሄደን ነበር፡፡ እንደተለመደው ናርዶስንም አገኘናት እና ብዙ ነገሮችን አጫወተችን፡፡“የተዘነጉት እስረኞች” እና የተዘነጋው የቤተሰቦቻቸው ስቃይ
ናርዶስ ትረካዋን የጀመረችው እናቷን እና ሌሎችም በተመሳሳይ መዝገብ ተከሰው የተፈረደባቸውን ሰዎች አያያዝ ነበር፡፡ ‹‹ሳስበው የተረሱ ያህል እየተሰማኝ ነው፤ ምክንያቱም ብዙ ጊዜ ሚዲያዎች ስለነሱ አይደለም እያነሱ ያሉት፡፡በእናቴ ክስ የታሰሩት ከ30 ሰዎች በላይ ናቸው፡፡ አንድ ሰሞን ከይቅርታ ጋር በተያያዘ ስማቸው እየተነሳ ነበር አሁን ግን ሁሉነገር የተረሳ ይመስለኛል›› በማለት የእስሩ ሕመም ለታሳሪዎቹ እና ለቤተሰቦቻቸው ግን የሚረሳ ዓይነት አለመሆኑን ነገረችን፡፡
‹‹ሚያዝያ 16፣ አርብ ቀን ነበር ሁሉም የተያዙት›› በማለት ሲታሰሩ የነበረውን ጠቅላላ ሁኔታ በማስታወስ ትጀምራለች፡፡ ‹‹ለአንድ ሰው የመጡ የማይመስሉ ብዙ ሲቪል የለበሱ እና የፌዴራል ፖሊስ ልብስ የለበሱ ፖሊሶች መሳሪያቸውን አቀባብለው ነበር ወደቤት የገቡት፡፡ ስልካችሁን አጥፉ ወደማንም እንዳትደውሉ አሉን፡፡ የብርበራ ማዘዣ ይዘው ነበር፤ ‹ቤት ልንፈትሽ ነው የመጣነው እማዋይሽ ዓለሙ በቁጥጥር ስር ውለሻል› አሏት ቤት ፍተሻው እስከ ምሽቱ አራት ሰዓት ድረስ ቀጥሏል፡፡ ቀኑ አርብ ነበር፤ እናቴ ደግሞ እስከ 12 ሰዓት ትጾም ስለነበር ከሥራ ወደቤት እንደገባች ‹ምግብ ስጡኝ› እያለች እያለ ነበር ፖሊሶች የገቡት ስለዚህ ምግብ ሳትበላ ውላ ነው ወደ እስርቤት የወሰዷት፡፡ ከዚያ በኋላ አራት ወራት ያክል ዓይኗን አላየነውም ነበር፤ ትሙት ትኑር የምናውቀው ነገር አልነበረም፡፡ ደግነቱ በሌላ ጉዳይ ታስራ በተፈታች ሴት አማካይነት መልዕክት ደረሰኝ፡፡ ‹አንቺ ደህና ከሆንሽ ሽሮ እና ጎመን ሰርተሸ አስገቢልኝ፤ እኔ ደግሞ ደኅንነቴነን የባናና ማስቲካ ወረቀት እልክልሻለሁ፡፡ ደኅና ካልሆንኩኝ ግን ያ ነገር ይቀራል› ብላ ላከችብኝ፡፡ ከዚያ እኔም ሽሮ እና ጎመን ሠርቼ በመላክ፣ እሷም የባናና ወረቀት በመላክ ደኅንነታችንን የሚገልፅ መልዕክት እንለዋወጥ ነበር፡፡ ይህ ሁሉ እየሆነ ባለበት ሰዓት እኛ በሌለንበት ጉዳያቸው ፍርድ ቤት ይታይ ነበር፡፡›› በማለት ጉዳያቸው በኢ ፍትሐዊ መንገድ በመንግሥት እንደተያዘ አጫውታናለች፡፡

Monday, April 29, 2013

ከፋውንዴሽኑ ጀርባ… (ክፍል ፩) – ከተመስገን ደሳለኝ | Zehabesha Amharic

ከፋውንዴሽኑ ጀርባ… (ክፍል ፩) – ከተመስገን ደሳለኝ | Zehabesha Amharic

የመለስ መታሰቢያ ተቋም (Foundation) የደቀነብን አደጋዎች! – ክፍል 1

የመለስ መታሰቢያ ተቋም (Foundation) የደቀነብን አደጋዎች! – ክፍል 1

ግጭቱን ማን ለኮሰው?




ቀኑ ማክሰኞ፣ ጥቅምት 22 1998 ዓ.ም፤ ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ገደማ… አንድ የከተማ አንበሳ አውቶብስ ተሳፋሪ ሳይጭን ከመርካቶ ተነስቶ ወደ ጎማ ቁጠባ አቅጣጫ በባዶ እየከነፈAddis Ababa, Ethiopia 2005 protest ቁልቁል ወርዶ ..ተ/ሃይማኖት ቤ/ክርስቲያን አደባባይን ከዞረ በኋላ ጥግ ይዞ ቆመ። ሹፌሩ አውቶብሱን ገትሮ ወዲያው ከአካባቢው ጠፋ። ለሁለት ሰዓት ገደማ አውቶብሱ እንደተገሸረ ቆየ።…በዚህ ቅፅበት አንዲት ነጭ ቶዮታ ፒካፕ (ታርጋ የሌላት ወይም ያለጠፈች) ከሱማሌ ተራ አቅጣጫ በከፍተኛ ፍጥነት እየከነፈች ከመጣች በኋላ < በላይ ተክሉ ኬክ> ቤትን አለፍ ብላ ቆመች። ከሹፌሩ ጎን ሲቪል የለበሰና ኮፍያ ያጠለቀ ሰው የተቀመጠ ሲሆን ከመኪናው ጋር ከተገጠመው ሬዲዮ መገናኛ በተጨማሪ ሁለት ተንቀሳቃሽ ስልኮችን ይዟል።… 25 ወጠምሻዎች፣ ሁሉም ረዘም- ወፈር ያሉ ዱላዎችን፣ ገሚሶቹ ደግሞ ገጀራ እንደጨበጡ እንዲሁም ከመካከላቸው ሁለቱ አነስተኛ ጀሪካን እንደያዙ…ከመኪናዋ ዘለው ወረዱ። ሁሉም የተቀዳደ ተመሳሳይ ድሪቶ አጥልቀዋል፤ « አደገኛ ቦዘኔ» መሆናቸው ነው። ነገር ግን « ሆን ተብሎ » የተዘጋጀ ድሪቶ እንደሆነ የሚያሳብቀው ….በግልፅ የሚታየው የሁሉም ፈርጣማ ጡንቻ ከጥሩ እንክብካቤ ጋር በስፖርት የዳበረና ወታደራዊ አቋም እንዲይዝ ተደርጎ የተገነባ መሆኑ ነበር።

Friday, April 26, 2013

ኣይጋ – ለአውራምባ አቀበለው – አውራምባ ደግሞ- ለትግራይ ኦንላይን!





ዑደቱ እንዲህ ይዞራል፡፡ ተረቱም እንዲህ ተለውጧል! «ትንሽ አሻሮ ይዘህ ከቆሎ ተጠጋ»፡፡ ወያኔን  ትንሽ እምት! እምት!  ትንሽ ቦጨቅ፥ ቦጨቅ፡፡ ከዚያም ተቃዋሚ መባል፡፡ ከተቃውሞው አምባ አድብቶ ገብቶ ደግሞ ቀበሮ  መሆን፡፡ ከዚያም እይጋ እየቆነጸለ የሚያወጣውን ትንሽ ለወጥ አድርጎ በአውራምባ ታይምስ ላይ ማውጣት፡፡ ገረብ ገረብ ትግራይ! መቃብረ አምሃራይን በተዘዋዋሪ አጠይሞ ማጮኽ፡፡
ከባለቤቴ ጋር ሆነን የአውራምባውን ዳዊት ከበደን የአከረባበት ስልት አንስተን ስንጨዋዋት ! እኔ ዳዊትን የገመገምኩባቸውን ነጥቦች ባለቤቴ በከፊል ተቀብሎ፣ ላይሆኑ ይችላሉ ያላቸውንም ነጥቦች አነሳሳልኝ፡፡ ዳዊት ወያኔ ሊሆን አይችልም አለኝ መሬት በደንብ ቆንጥጦ፡፡ ለምን አይሆንም አልኩት? ከቅንጅት መሪዎች ጋር አብሮ ሁለት አመት ታስሮ አለኝ፡፡ ብዙ ጊዜ ዞምቢዎች ያሞኙሃል አልኩት፡፡ የባለቤቴን የዋህነቱን ስለማቅ!
የዶክተር አረጋዊ በርሄን መጽሃፍ አንብበህ የለ? ወያኔ እኮ የጦርነት ልብሳቸውን አስወልቆ፣ ኮበሌዎቹን የመነኩሴ ልብስ አስለብሶ ዋልድባ የከተተ መንግሥት ነው፡፡ ለዓላማቸው ቋርፍ እየበሉ፣ ቀኑ ሲደርስ ዋልድባን ያሳረሱት እኮ የወያኔ መነኩሴዎች ናቸው፡፡ ይህ እንዴት ተዘነጋህ ? ለዚያውም ገዳም ውስጥ ሃያ አንድ አመት ችሎ መክረም የሚችሉ ናቸው እንኳን ቃሊቲ ሁለት ዓመት አልኩት፡፡ ለዓላማህ ስትል ቃሊቲ ሁለት ዓመት ብትታሰር ምንድነው? ለዚያውም ጥሩ ጥሩ «ኡፋ» እየጠለፍክ አልኩት፡፡

Wednesday, April 24, 2013

የህወሀት ደህንነቶችን ጤና የነሳው የፌስቡክ ጦማር



በህወሀት/ኢህአዴግ ውስጥ መግባባት ጠፍቷል፣ የወያኔ ቁንጮዎች ወዴት እንደሚሄዱ አያውቁም። እንደው በደፈናው “የመለስ ዜናዊ ራዕይ” ይበሉ እንጂ ራዕዩን እነርሱም አያውቁትም። ካድሬውም ሹማምንቱም እርስ በርስ ተናንቋል። በዚህ ሁኔታ ላይ እያሉ ሁኔታቸውን ህዝብ እንዳያውቅባቸው እያደረጉ ያሉት ጥረት እምብዛም የሰራ አይመስልም። የሙስሊሞች ተቃውሞ እንደቀጠለ ነው፣ በአማራ ብሄር ተወላጆች ላይ የሚደርሰው ግፍ ህዝቡን ከዳር እስከዳር አስተባብሯል/ቀስቅሷል፣ ምርጫውን ምርጫ ለማስመሰል ያደረጉት ጥረት አልተሳካም፣ ጋዜጠኞች እና የፖለቲካ እስረኞች እንዲፈቱ አለማቀፉ ማህበረሰብ እና ኢትዮጵያውያን ከፍተኛ ጫና ፈጥረዋል። ለዚህም ይመስላል የወያኔ የደህንነት ሹሞች የሀሰት ዜናዎችን በፌስቡክ እያሰራጩ ፋታ ለማግኘት የሚጣጣሩት። ከዚህ በታች አብረሃ ደስታ ከመቀሌ በፌስቡክ የለቀቀውን ጦማር፣ የህወሃት/ኢህአዴግን ወቅታዊ አቋቋም እንደወረደ አቅርበነዋል።

በህወሓት የጉባኤ ኣጀንዳ ዙርያ ስብሰባ ሊጠራ ነው

አብረሃ ደስታ፣ ከመቀሌ
ከኢህኣዴግ ጉባኤ በኋላ መሪዎቻችን (ከበፊቱ ብሶባቸው) መግባባት ኣቅቷቸዋል። በፌደራል ደረጃ የሚደረጉ ስብሰባዎች ያለ ዉጤት ይጠናቀቃሉ። ለምን ኣይግባቡም? (‘ቀሽምEthiopian blogger Abraha Desta from Tigry, Mekele ጥያቄ’)። የሚያግባባ ነጥብ የላቸውማ። ድሮ (ከ‘ባለራእዩ መሪ’ ዕረፍት በፊት) ሁሉም ነገር እሳቸው ይሰሩት ስለነበር) በመሪያቸው ነበር ‘የሚግባቡት’ (አብረው የሚጓዙ)። በሰው ‘ይግባባሉ’ (ሌላ ሊያግባባቸው የሚችል ሓሳብ ወይ መርህ አልነበራቸውም፣ የላቸውም)። አሁን ታድያ እንዴት ይግባቡ?
‘ባለራእዩ’ ሰውዬ መመርያ ይሰጣል፣ ‘ፖሊሲ ነው ተግብሩት’ ይላቸዋል፣ እነሱም እሱ የተናገረውን ‘ቃል’ እየደገሙ (ከላይ እስከ ታች) ይዘምራሉ። ስሕተት መሆኑ (ሊተገበር የማይችል መሆኑ) ሲረዱ ‘ስሕተቱ ያለው አፈፃፀም ላይ ነው’ ብለው ራሳቸው ያፅናናሉ። ህዝቡ በማይፈፀሙ ፖሊሲዎች ተስፋ እንዳይቆርጥ መሪዎቻችን ሁሌ ስለ አዲስ ፖሊሲ ወይ አሰራር ይሰብካሉ። ሁሌ ስለ ‘አዲስ ኣሰራር’ ወይ ዕቅድ ሲወራልን ለውጥ የመጣ ያህል እንዲሰማን ለማድረግ ያህል ነው።

Sunday, April 21, 2013

ኢህአዲግ (ወያኔ) የአባይን ግድብ የቦንድ ሽያጭ በባህር ማዶ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንን መተንኮሻ አድርጎታል




ዛሬ እነሆ በኖርዌይ እንዲህ ሆነ
Ethiopians in Norway protest, April 2013

ከኖርዌይ ከተሞች ውስጥ በደቡባዊ ክፍል የምትገኘው ስታቫንገር ከተማ ዛሬ ሚያዝያ 12/2005 ዓም በስዊድን የኢትዮጵያ አምባሳደር ወ/ሮ መብራት በተገኙበት ለአባይ ግድብ ቦንድ ሽያጭ የተዘጋጀው ዝግጅት ከኦስሎ ከ ስምንት ሰዓታት በላይ በአውቶቡስ ተጉዘው በስብሰባው በተገኙ ኢትዮጵያውያን በገጠመው ከፍተኛ ተቃውሞ ሙሉ በሙሉ ዝግጅቱ ተሰርዞ አምባሳደሯ በፖሊስ ቦታውን ለቀው  እንዲሄዱ ተመክረው አዳራሹን ለቀው ወጥተዋል።

Breaking News: Ethiopians in Norway Chased TPLF Ambassador


Norway police stopped meeting in Tasta Bydelshus  

The police came out with three cars and six policemen and stopped a meeting of Tasta bydelshus where the atmosphere was becoming so very irritably among the more than 300 Ethiopian origin attendees.
The 300 attendees were Ethiopian asylum seekers or people with Ethiopian background. The police feared that it would get completely out of control when people in the audience went to the hard verbal confrontation against two representatives from the Ethiopian Embassy in Stockholm who had called for and chaired the meeting.

Monday, April 15, 2013

ዲሞክራሲ !

                               

   ዲሞክራሲ !!!

                                  

                                            በዜማ  እንጉርጉሮ በግጥም ደርድሮ
                                            ያልዘከረሽ ማነው አንቺን ስንኝ ቛጥሮ
                                            ወረቀት   ከብእር   ያገጣጥምና
                                            ያወዳድስሻል ቀለም ያፈስና ፥
                                            እጫኛሽ ብዛቱ ቀለበት አሳሪው
                                            በፍቅርሽ   ታማሚው
                                            ለሶስት አራት ቀን ጫጉላ ቤት አዳሪው

Sunday, April 14, 2013

እነ ማን ነበሩ? አሁንስ ማን ናቸው?




ይህ ጽሑፍ ትኩረት የሚሰጠው በትግል በረሃ በነበርንበት ወቅት ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህ.ወ.ሓ.ት.) በክርስትና እና በእስልምና ሃይማኖቶች ላይ ሲከተል የነበረውን አቋሙን
Gebremedhin Araya former TPLF
አቶ ገብረመድህን እርአያ
ተቀብሮ ከነበረበት ጉድጓድ አውጥቼ ለኢትዮጵያ ሕዝብ እነማን ናቸው የሚለውን ታሪካቸውን እና የተፈጸመውን ጸረ-እምነት ግፍ በአጭሩ ለማሳወቅ ነው።
ህ.ወ.ሓ.ት. ገና ሲፈጠርና ተ.ሓ.ህ.ት. ተብሎ እንደተመሰረተ ሙልጭ ያለ ጸረ-ዲሞክራሲ ድርጅት ነው። በጸረ-ኢትዮጵያነትና በጸረ- ሕዝብነት የተሰማራ ቅጥረኛ ድርጅት መሆኑን ብዙ ጊዜ በጽሑፍና በተለያዩ መገናኛ ብዙሃን ለኢትዮጵያ ህዝብ ተናግሬአለሁ። የአሁኑ ጽሑፌ ህ.ወ.ሓ.ት. በሃይማኖት ላይ ሲከተለው የነበረውን ፖሊሲ ገና ከመጀመሪያ ትግሉ አንስቶ እስከ አሁን ድረስ የነበረውን ጸረ- ሃይማኖት ተግባራቱን የኢትዮጵያ ሕዝብ በግልጽ አውቆታል። እኔ ደግሞ የራሴን ልበል።
በ1969 መጀመሪያ ጀምሮ “ወይን” በሚለው የድርጅቱ ልሳን መጽሔት ላይ በተደጋጋሚ “የክርስትና ሃይማኖትና አማራው” በሚል ርእስ ተጽፎ የሚወጣው ጽሑፍ፣ “የክርስትና ሃይማኖት የአማራው ዋና መሳሪያና የግዛቱን ህልውና ማስጠበቂያ ነው፣ በመሆኑም የትግላችን ጠላት አማራውና መሳሪያው የተዋህዶ ክርስትና ስለሆኑ አብረው እንዲጠፉ ማድረግ አለብን” እያለ ያትት ነበር። ይህንን መጽሔት በሰፊው ለታጋዩና ለአባላቱ በማሰራጨት ሰፊ ቅስቀሳ አካሂዶበታል። በነሐሴ 1969 “ወይን” መጽሔት አማርኛ ቋንቋም አብሮ መጥፋት እንዳለበት ሃተታ ይዞ ወጥቷል።

ዘር ማጥራትን ያህል ወንጀል ፈጽሞ ይቅርታ መጠየቅ ፌዝ ካልሆነ ድራማ ነው


Amhara Ethnic group members Ethiopia
በፌዴራል ስም የተሸፈኑ ህውሃት/ኢህአዴጎች እና በአቶ መለስ ራዕይ የተጠመቁ የክልል ፖለቲከኞች በኢትዮጵያ የዘር ማጥራት (Ethnic Cleansing) ወንጀል ስለመፈጸማቸው መዘገብ ከጀመረ ውሎ አድሯል። ይኽ ዜና በኢትዮጵያ ወዳጆች ኢትዮጵያውያን እና የውጭ ዜጎች ዘንድ ስጋት ፈጥሯል። ኢትዮጵያ እንድትበተን የሚፈልጉ ግን አፍና እጃቸውን አስተባብረው ኢትዮጵያ የምትባል አገር ከመንገዳቸው ላይ ተወግዳ ህልማቸው ወደሆኑት የቃል-ኪዳን አገሮቻቸው (Promised-land) ለመድረስ የጀመሩትን ጉዞ ፍጥነት እና ግልጽነት ሳያመቻቸው ዝቅ ሲያመቻቸው ደግሞ ከፍ ያደርጋሉ እንጂ አያቆሙም። የህውሃት ሕገ መንግስት (አንቀጽ 39) ግፉ በርቱ ይላል። ስለዚህ የቤንሻንጉል ጉምዝ አስተዳዳሪ አቶ አህመድ ናስር ቀደም ብሎ በቪኦኤ አማርኛ ፕሮግራም ሲጠየቅ አፉን ሞልቶ ሞቅ ባለ ስሜት አማርኛ ተናጋሪውን ያፈናቀልነው መሬቱን ለልማት ስለፈለግነው ነው እንዳላለ ሁሉ ድንገት ተነስቶ ሰሞኑን ይቅርታ መጠየቁ ማጭበርበሪያ ድራማ እንጂ ሃቅ አይደለም። ይኽ ይቅርታ ከራዕይ እና ከፖሊሲ ለውጥ የመነጨ ሳይሆን የተለመደው የህውሃት ማዘናጊያ እና አቅጣጫ ማስቀሪያ ፕሮፖጋንዳ ነው። ለአንድ ደቂቃ እንኳን መዘናጋት የለብንም። ላብራራ።

Monday, April 8, 2013

የህወሓት/ኢሕአዴግ የዘር ማጽዳትና የዘር ማጥፋት ዘመቻ በአስቸኳይ መቆም አለበት!



የኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓ)
Ethiopian People’s Revolutionary Party (EPRP) (ዴሞክራሲያዊ/Democratic)
ዜጎች በሀገራቸው ውስጥ በመረጡት ሥፍራ የመኖር፤ ሠርቶ ሃብት የማፍራት፤ ቤተሰብ የመመሥረት…ወዘተ በማንም ሊሰጣቸው ወይም ሊነፈጋቸው የማይችል ሁለንተናዊ የዜግነትEthiopian People's Revolutionary Party (EPRP Democratic)መብቶቻቸው ናቸው። ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ግን በዓለማችን የተነሱ የጎሣ እንቅስቃሴዎች ሁለንተናዊ የዜጎችን መብቶች በሚፃረር መልኩ አንድ-ወጥ የሆነ ወይም ከሌሎች ዘር የፀዳ ሀገርና መንግሥት ለመፍጠር ጥረዋል። ዓላማቸውን ሊያሳኩ ባልተቻሉባቸው ኅብረብሄር በሆኑ አገሮች ውስጥ ደግሞ የኤኮኖሚ፤ የፓለቲካና የወታደራዊ ኃይሉን በአንድ ዘር የበላይነት ለመያዝ ሲባል የዘር ማጽዳት ዘመቻ (ኤትንክ ክለዚንግ)ና የዘር ማጥፋት ዘመቻ (ጄኖሳይድ) ወንጀል መፈጸም የተለመደ ክስተት ሆኗል።
በዘጠናዎቹ መጀመሪያ ላይ የምሥራቁ የሶሻሊስት ካብ በተፈረካከሰበትና የሥልጣን ክፍተት በተፈጠረበት ወቅት፤ እነዚህ የጎሣ የወንጀል ቡድኖች በሕዝብ ውስጥ የነበሩ የፍትህ፤ የእኩልነትና የነፃነት ትክክለኛ ጥያቄዎችን በማጣመምና ለራስ እኩይ ዓላማ በማዋልና ሕዝብን በማሳሳት የጎሣ ወታደራዊ ኃይሎችን በማቋቋም አሰቃቂ የዘር ማጽዳትና የዘር ማጥፋት ወንጀሎችን ፈጽመዋል። ዓለምአቀፍ የዜና ሽፋን ባገኙት ሀገሮች፤ ለምሳሌ በዩጎዝላቪያ፤ በሩዋንዳ፤ በኮንጎ፤ በሱዳን….ወዘተ ወንጀለኞቹ በዓለምአቀፍ ፍርድ ቤት መፈለጋቸውና አንዳንዶቹም ተይዘው ለፍርድ በመቅረባቸው ዘግናኝ ወንጀላቸውን እንዲያቆሙ ወይም እንዲሰወሩ አድርጓቸዋል። እንደ ኢትዮጵያ ባሉ ሀገሮች ግን ዓለምአቀፍ የመገናኛ ብዙሃን ሽፋን ባለማግኘታቸው ወንጀሉ አሁንም በማንአለብኝነት በሰፊ እየተካሄደ ነው።

ትግል… ሽንፈት፤… ድል፤ ሽንፈት…


Temesgen Desalegn Feteh newspaper editorከምሽቱ አንድ ሰአት አልፏል፤ የእጅ ስልኬ ደጋግሞ ቢጮኽም ትኩረት አልሰጠሁትም፡፡ ከጥቂት ሰከንዶች ፋታ በኋላ የቢሮዬ ስልክ ጮኸ፤ አነሳሁት፡፡ ለካስ እንዲህ በአንዱ አልመልስ ስላት፣ በሌላው እያፈራረቀች የምትደውለው ዕድሜዋ ወደ ሰባ እየተጠጋ ያለው አሮጊቷ እናቴ ኖራለች፡-
‹‹አቤት! እናቴ››
‹‹ለምንድነው የዚህን ያህል ስልኩ ሲጮኽ የማትመልሰው?›› ቆጣ ብላ ጠየቀችኝ፡፡
‹‹አስቸኳይ ስራ ላይ ስለነበርኩ ነው››
‹‹ኤዲያ! አንተ ደግሞ ሁል ጊዜ ጠብ ለማይል ነገር፣ ችክ ማለት ትወዳለህ››
…በእርግጥ እናቴ እውነቷን ነው! ችክ ያልኩ ቸካካ ነገር ሳልሆን አልቀርም ፡፡
‹‹ልዕልና›› ጋዜጣ ታግዳለች፤ እንደ‹‹ፍትህ›› እና ‹‹አዲስ ታይምስ›› ሁሉ የስርዓቱ የአፈና ሰለባ ሆናለች፤ የሚገርመው ግን መታገዷ አይደለም፣ የታገደችበት መንገድ እንጂ፡፡ ከዚህ ቀደም ደጋግሜ እንደገለፅኩት አቶ መለስን የተኩት ሰዎች ከእረሱም የባሱ ጭፍን አምባገነኖች ናቸው፡፡ ማንንም አይፈሩም፡፡ እግዚአብሄርንም ቢሆን ‹‹በአብዮታዊ ዲሞክራሲ ካልተጠመቅህ አምላክ ሆነ እንድትቀጥል አንፈቅድልህም›› ከማለት አይመለሱም፡፡

ወያኔ በአማራ ተወላጆች ላይ የጀመረውን የዘር ማጥፋት ዘመቻ እንደቀጠለ ነው



ወያኔ ለአማራ ህዝብ፤ ባህልና ታሪክ ያለዉን ጥላቻ ከተራ ጥላቻ አልፎ በተግባር አማራዉን ወደ ማጥቃት ዘመቻ አደገ እንጂ ለአንድም ቀን ቀንሶ አያውቅም። አማራው እንደ ሰው ልጅ የመኖር መብቱ፣GINBOT 7 Movement ስብእናው ተገፎ ከቀየው፣ ከመንደሩ የአፈራውን ንብረትና ገንዘብ እየተቀማ መባረሩ፣ መሰደዱ፣ እንግልቱ ሁሉ የወያኔ የበቀል እርምጃ ነው።
በአሶሳ፤ በደኖና በአርባጉጉ ውስጥ አማራ በመሆናቸዉ ብቻ ህጻናት፤ሴቶችና አረጋዉያን በግፍ ተገድለዋል። ባለፈዉ አመት በደቡብ ክልል ጉራ ፈርዳ እየተባለ በሚጠራዉ አካባቢ ለረጂም አመታት ከአካባቢዉ ኢትዮጵያዊ ወገናቸው ጋር ተግባብተዉ ይኖሩ የነበሩ የአማራ ብሄረሰብ አማራ በመሆናቸዉ ብቻ ለአመታት ያፈሩትን ንብረት ይዞ የመሄጃ ግዜ እንኳን ሳይሰጣቸዉ አከባቢዉን ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ለቅቀዉ እንዲወጡ እንዲፈናቀሉ ተደርጓል።
ከመጋቢት ወር መጀመሪያ ጀምሮ ወያኔ በአማራዉ ህዝብ ላይ አዲስና ሰፋ ያለ የጥቃት ዘመቻ ጀምሯል። በደቡቡ የአገራችን ክልል በጉራፈርዳ የጀመረዉን አማራውን ነጥሎ የማጥቃትና የማንገላታት ዘመቻ አሁን ደግሞ በሰሜን ምስራቅ የአገራችን ክፍል በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ቀጥሏል።

የችግራችን ጥልቀቱ – መክፈቻው መጥፋቱ



ዘግይቼ ነበር ይህን ጹሑፍ ከከረነት ያዬሁት „የሲፒጄውን ተሸላሚ” ዳዊት ከበደን መጨረሻ ማየት ናፈቀኝ ከጸሐፊ ክፈሌ ስንሻው አኔሳ“
እኔ ብዙም ድህረ ገፆችን አልጎበኝም። ውስኖችን ነው የማያቸው። አውራንባ ታይምስን ለመጀመሪያ ጊዜ አሁን ገብቼ አዬሁት። የቀረበውን መረጃና የተሰጠውን አሰተያዬት ማገናዘብ ስለነበረብኝ። ኢሳት መኖሩ፤ መፈጠሩ የሚያንገበግባቸው የመኖራቸውን ያህል የሚያስደስታቸው ወገኖች ደግሞ እንዳሉ ከተሰጡት አስተያዬቶች ማንበብ ችያለሁ። ሁሉም የራሱን፤ የሚመስለውን፤ የግሉን አስተያዬት መስጠቱ መብት ነው። ነፃነት ፈላጊነታችን የሚለካበት፤ የሚሰፈርበት፤ የሚመዘንበት መሰፈርቱ ይህ ነውና። ዕድሉ ቢኖረን ይህን መሰል ነፃነት መስጠት ካልቻልን … ?!
በነፃነት ሕይወት ውስጥ የማይመቸውንም ተቀብሎ ተስማምቶ መኖር። በነፃነት ፍቅር ውስጥ ሁሉም የውስጡን ዘርግፎ እራሱን አስጎብኝቶ፤ ወደ አንድ የሚያስማማ፤ የሚያገናኝ፤ መስመር መጓዝ እንዲችል የፍቅር ሐዲድ መዘርጋት ነው። የሚሰጡ ትችቶች፤ የሚጠቀሱ ድክመቶች፤ የሚጠረቡ አስተያዬቶችን ተከታትሎ በአዎንታዊ ዕይታ ሊስተካከሉ የሚገባቸውን በማስተዋልና በመርመር፤ ሊታረቁ የሚገባቸውን በትእግስት በማስታረቅ፤ የተዛቡትን በአዎንታዊ ቅን ዕይታ በማረቅና በማስተካክል ወደሚፈለገው አቅጣጫ ማቅናት የሚፈለግ ሲሆን፤ ይህንንም ወደነውና ከልብ ተቀብለነው ልናሳተናግደው የሚገባ ክስተት ሊሆን ይገባል። ከሁሉ በላይ ልምድና ተመክሯችን ከግብታዊነት ሊያድን እንዲችል በፍጹም ልቦናችን ልንፈቅድለት ይገባል።

Eskinder is a hero to the world but a villain to Meles Zenawi and his disciples



Right in Prison, Wrong on the Throne


Last April, I wrote a “Special Tribute to My Personal Hero Eskinder Nega”.  In that tribute, I groped for words as I tried to describe this common Ethiopian man of uncommon valor, an ordinary journalist of extraordinary integrity and audacity.
Standing with Ethiopia's tenacious blogger, Eskinder Nega - CPJ blog
Eskinder Nega
Frankly, what could be said of a simple man of humility possessed of indomitable dignity? Eskinder Nega is a man who stood up to brutality with his gentle humanity. What could I really say of a gentleman of the utmost civility, nobility and authenticity who was jailed 8 times for loving liberty?  What could I say of a man and his wife who defiantly defended press freedom in Ethiopia, even when they were both locked up in Meles Zenawi Prison just outside of the capital in Kality for 17 months! What could anybody say of a man, a woman and their child who sacrificed their liberties, their peace of mind, their futures and earthly possessions so that their countrymen, women and children could be free!?
Ethiopian journalist Eskinder Nega is a special kind of hero who fights with nothing more than ideas and the truth. He slays falsehoods with the sword of truth. He chases bad ideas with good ones. Armed only with a pen, Eskinder fights despair with hope; fear with courage; anger with reason; arrogance with humility; ignorance with knowledge; intolerance with forbearance; oppression with perseverance; doubt with trust and cruelty with compassion. Above all, Eskinder speaks truth to power and to those who abuse, misuse, overuse and are corrupted by power.