Monday, December 17, 2012

ኢትዮጵያ ዘመናዊ የህፃናት የውጭ ንግድ





የጉዲፈቻ ታሪክ በኢትዮጵያ በባህላዊ መንገድ ሲደረግ የቆየ ነው መቼ 
እንደተጀመረ በእርግጠኝነት ለማወቅ ባይቻልም በ18 ክፍለ ዘመን በኦሮሞ 
ብሔረሰብ እንደተጀመረ ይታሰባል። ጉዲፈቻ የሚለው ቃል የመጣው ከኦሮሚኛ 
ቋንቋ ሲሆን ትርጓሜውም ተፈጥሮዓዊ የወላጅነትና የልጅነት የሥጋ ዝምድና 
ሳይኖር ከሌላ ሰው አብራክ የተወለደን ልጅ ኢኮኖሚያዊ ማህበራዊ ጥቅሙን 
ጠብቆ እንደ አብራክ ክፋይ ልጅ ማሳደግ ማለት ነው። በኢትዮጵያ የጉዲፈቻ 
ሕግ ለመጀመሪያ ጊዜ በ1952 ዓ.ም በወጣው የፍትሐብሔር ሕግ ማዕቀፍ 
ተሰጥቶታል ይህም ሕግ የሕፃኑን መብት የሚያስጠብቅ ሆኖ የተዘጋጀ ነው።