Monday, December 17, 2012

ኢትዮጵያ ዘመናዊ የህፃናት የውጭ ንግድ





የጉዲፈቻ ታሪክ በኢትዮጵያ በባህላዊ መንገድ ሲደረግ የቆየ ነው መቼ 
እንደተጀመረ በእርግጠኝነት ለማወቅ ባይቻልም በ18 ክፍለ ዘመን በኦሮሞ 
ብሔረሰብ እንደተጀመረ ይታሰባል። ጉዲፈቻ የሚለው ቃል የመጣው ከኦሮሚኛ 
ቋንቋ ሲሆን ትርጓሜውም ተፈጥሮዓዊ የወላጅነትና የልጅነት የሥጋ ዝምድና 
ሳይኖር ከሌላ ሰው አብራክ የተወለደን ልጅ ኢኮኖሚያዊ ማህበራዊ ጥቅሙን 
ጠብቆ እንደ አብራክ ክፋይ ልጅ ማሳደግ ማለት ነው። በኢትዮጵያ የጉዲፈቻ 
ሕግ ለመጀመሪያ ጊዜ በ1952 ዓ.ም በወጣው የፍትሐብሔር ሕግ ማዕቀፍ 
ተሰጥቶታል ይህም ሕግ የሕፃኑን መብት የሚያስጠብቅ ሆኖ የተዘጋጀ ነው።

Monday, November 26, 2012

የሰማዕቱ የአቡነ ጴጥሮስ ሐውልት ለባቡር ሀዲድ ግንባታ ሲባል ይፈርሳል መባሉ ከፍተኛ ህዝባዊ ቁጣ ቀሰቀስ


ኢሳት ዜና:-መንግስት በበኩሉ  ሐውልቱ ለደህንነቱ ሲል ከተነሳ በሁዋላ ወደነበረበት ስፍራ ይመለሳል እያለ ነው።
በአዲስ አበባ ውስጥ ሊሠራ በታቀደ የ ከተማ ውስጥ የባቡር  ሀዲድ ሥራ ምክንያት  የዓፄ ምኒልክና የአቡነ ጴጥሮስ ሐውልት ሊፈርሱ የመቻላቸው ወሬ  አስቀድሞ የሾለከው ፤ለምድር ባቡር ኮርፖሬሽን ቅርበት ካላቸው  ምንጮች  ነው።
እነዚህ የዘርፉ ሙያተኞች በ አምስት ዓመቱ የልማትና የትራንስፎርሜሽን ዕቅድ መሰረት በ አዲስ አበባ ውስጥ ሊዘረጋ የታሰበው የባቡር ሀዲድ ፕላን  የዳጋማዊ አፄ ምኒልክንና የ አቡነ ጴጥሮስን ሐውልት እንደሚነካ በመጥቀስ፤ በተለይ የጣሊያንን ወረራ አልባርክም በማለታቸው ሳቢያ በመትረየስ ተደብድበው የተገደሉት የ አቡነ-ጴጥሮስ  ሐውልት ሙሉ በሙሉ እንደሚፈርስ ተናግረዋል። ዜናውን የሰሙ እጅግ በርካታ ኢትዮጵያውያንም በተለያዩ ማህበራዊ ገፆች ተቃውሟቸውን ማሰማት ጀምረዋል።

የአሻንጉሊቱ “ፍርድ ቤት” ራሱን እንደገና አዋረደ!



የወያኔ አገዛዝ ከፍርድ ቤትት ወደ ተራ የፖለቲካ ማጥቂያ መሳሪያነት የለወጣቸዉ የኢትዮጵያ ፍርደ ቤቶች የዕለት ከዕለት ዉርደት አሁንም እነደቀጠለ ነዉ። ሃያ አመት ሙሉ አገዛዙ የወነጀላቸዉነ እየኮነነና አገዛዙ አሸባሪ ያላቸዉን በሽብርተኝነት ፈርጆ አስራትና የሞት ፍርድ ሲፈርድ የከረመዉ የወያኔዉ ፍርድ ቤት ከሰሞኑ ሙሉ ኃይሉን ወደ ኦሮሞ ህዝብ በማዞር የኦርሞ ፌዴራሊስት ዲሞክራቲክ ንቅናቄ (ኦፈሰዴን)ና  የኦሮሞ ህዝብ ኮንግሬስ ፓርቲ ከፍተኛ አመራር አካል አባል  የሆኑትን አቶ በቀለ ገርባንና አቶ ኦብላና ሌሊሳን ኦነግን ትረዳላችሁ የሚል ሰንካላ ምክንያት ፈጥሮ ወነጀለኛ አድርጓቸዋ ል። 

የትግራይ ህዝብን ማታለል ይብቃ! በቃ!



በትግራዩ ህዝባችን ስም የሚደረገው ንግድ አሁንም ከ21 የግፍና የከፋፍለህ ግዛ አመታት በኋላ ተባብሶ እንደቀጠለ ነው።ዘረኛውየወያኔ ቡድን ህወአት “እውነት እውነት እላችኋለሁ መለስ ከመሞቱ በፊት ለትግራይ ህዝብ ያስቀመጠው ጣፋጭ ከረሚላ እና ዝም በሉ” ሲሉ ይደመጣሉ::
የትግራይ ህዝብ እንደ ሌላው የኢትዮጵያ ህዝብ የስርአቱ የስቃይ፣ የሰቆቃ፣ የስደት፣ የግድያና የእስራት ገፈት ቀማሽ ነው። ከጥቂት የሕወአት ጎጅሌዎች በስተቀር! ታዲያ ይህንን እውነት በጠራራ ጸሃይ ላይ በህወአት/ወያኔ የጨለማ ዘመን የሚኖረውን ምስኪኑን የትግራይ ህዝብ ለመካድ እና እንደ ህጻን ልጅ የሚጣፍጥ ከረሚላ አዘጋጅተንልሃል እና ስለዲሞክራሲ ስለነጻነት አትናገር አትጠይቅ ዝም በል አታልቅስ በሚል የማታለል ስራቸውን አሁንም በማደስና ተግባራዊ ለማድረግ በአምባገነኑ የሟቹ ባለቤት አዜብ መስፍን አማካኝነት የትግራይ ህዝብን ለመስበክ ያስባሉ።

Sunday, November 11, 2012

34 ፓርቲዎች በ2ዐዐ5 ዓም በሚካሄደው ምርጫ ለምርጫ ቦርድ ያቀረቡት ጥያቄ


                                                                                                                ጥቅምት 29 ቀን 2ዐዐ5 ዓ.ም
ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ጽ/ቤት
አዲስ አበባ

ጉዳዩ፡- ጥቅምት 15 ቀን 2ዐዐ5 ዓም በአዳማ ከተማ ቦርዱ ‹‹በ2ዐዐ5 ዓም በሚካሄደው የአካባቢ ምርጫ አፈፃፀም
የጊዜ ሰሌዳ ረቂቅ›› ላይ ከፖለቲካ ድርጅቶች ከፍተኛ አመራሮች ጋር ባአደረገው ምክክር ፕሮግራም ተገኝተው
ፔቲሽን ከፈረሙ የፖለቲካ ፓርቲዎች የቀረበ ጥያቄ ስለማቅረብ፣

Ethiopia woman tells of sex slavery in Saudi Arabia



 | 11 November 2012 |
ADDIS ABABA: An Ethiopia woman revealed that she was the victim of sex slavery after she attempted to find work as a domestic worker in Saudi Arabia.
(Picture: Ethiopian women face massive hardships, including sexual violence in Saudi Arabia.)
For H, who asked that her identity remain anonymous, her ordeal began after she took a boat to

‹‹ናፍቆት እኔ ብሞትም አንተ ንብረቴን ታስመልሳለህ›› እስክንድር ነጋ


(በጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ) ከነገ በስቲያ (ማክሰኞ ህዳር አራት) በከፍተኛው ፍርድ ቤት ሶስተኛ ወንጀል ችሎት የእስክንድር ነጋን ንብረት ለመውረስ ይሰየማል፡፡
በትላንትናው ዕለት የክስ ቻርጅና መንግስት እወርሳቸዋለሁ ያላቸውን የእስክንድር ሁለት ቤቶች ካርታ የተያያዙበት መጥሪያ ደርሶታል፡፡ (በነገራችን ላይ መንግስት ሊወስዳቸው ከተዘጋጁት ቤቶች አንዱ በእናቱ ስም ያለ ሲሆን የዛሬ ዓመት አካባቢ ባለቤቱ ጋዜጠኛ ሰርካለም ፋሲል የቤቱን ስም ለማዞር ፈልጋ ‹‹ካርታው የለም›› በሚል አንዴ ቀበሌ፣ ሌላ ጊዜ ክፍለ ከተማ፣ ቀጥሎ አዲስ አበባ መስተዳደር ስትመላለስ ከርማ ሊገኝ ስላልቻለ ሰልችቷት ትታው ነበር፡፡ ትላንት ግን ዓቃቢ ህግ ከክስ ቻርጁ ጋር አያይዞ አቅርቦታል፤ እናም ምንአልባት ያን ግዜ ‹‹ካርታው የለም›› የተባለው ሆነ ተብሎ ተደብቆ ሊሆን ይችላል)

Saturday, November 10, 2012

የአዲግራት እስር ቤት ተደርምሶ 14 እስረኞች ሞቱ



(ሪፖርተር ጋዜጣ)

ከኢትዮሚድያ ዝግጅት ክፍል - ኢትዮሚድያ ይህን ዜና ከሪፖርተር ጋዜጣ አንድ ቀን ቀደም ብሎ መዘገቡ ይታወሳል (በእንግሊዝኛ
የተጻፈው ዜና ከታች ይመልከቱ):: የአደጋው መንስኤ ምንድነው ብሎ ሪፖርተር የትግራይ ክልልን ባለስልጣናት ጠይቆ ነበር።ሆኖም
ለመናገር ፈቃደኞች ሳይሆኑ ቀርተዋል። እንደ ኢትዮሚድያ ዘገባ ከሆነ ግን የኢትዮጵያ አንድነትና ነፃነት ኃይል (Ethiopian Unity
and Freedom Force – EUFF) ለጥቃቱ ተጠያቂ እኔ ነኝ ሲል አስታውቋል።

Thursday, November 8, 2012

ኢህአዴግ ስንት ቦታ ሊሰነጠቅ ይችላል?



  (ከተመስገን ደሳለኝ)

ብርዱ የጥቅምት ነው፤ አጥንት ድረስ ዘልቆ የሚያንቀጠቅጥ ኃይለኛ ቅዝቃዜ፡፡ አዲስ አበባ ገና ከእንቅልፏ
በመንቃት ላይ ነች፡፡ ለስራ የቸኮሉ መንገደኞች ትራንስፖርት ፍለጋ ወዲያ ወዲህ ይካለባሉ፡፡ ማክሰኞ
ጥቅምት 7 ቀን 2005 ዓ.ም. ከጠዋቱ 12 ሰዓት ከ50 ደቂቃ ላይ ብስራተ ገብርኤል አደባባይ ‹‹መገናኛ
ራዲዮ›› በያዙ የትራፊክ ፖሊስ አባላት በቁጥጥር ስር ዋለ፡፡ የትራፊክ ፖሊሶቹ ስራ የበዛባቸው ይመስላሉ፡፡
12 ሰዓት ከ55 ደቂቃ ሲል በሁለት የሞተር ብስክሌት በተፈናጠጡ የትራፊክ ፖሊሶች ፊት አውራሪነት
አንዲት ሳይረን የተገጠመላት የፖሊስ ታርጋ የለጠፈች መኪና የ‹‹መንገድ ልቀቁልኝ›› ጩኸቷን እያንባረቀች
አቋርጣ በማለፍ ወደ ሳር ቤት አቅጣጫ ከነፈች፡፡ ሶስት ‹‹ቪኤት›› መኪና ሰለሱ፡፡ ሌላ ባለሳይረን መኪናም
ከኋላ እየተከተለች ነው፡፡ ሁሉም መኪኖች በከባድ ፍጥነት ነው የሚበሩት፡፡ ሳር ቤት ያለው የፑሽኪን
አደባባይም ተመሳሳይ ቁጥር ባላቸው የትራፊክ ፖሊሶች ተጨናንቋል፡፡ ሜክሲኮ አደባባይ፣ አምባሳደር፣ ፍልውሃ፣ ገብርኤል መሳለሚያ…

የእንክርዳድ ውርስ


የእንክርዳድ ውርስ
ክፍል ፩
/The Inheritance of Chaffs/
/Part-I/
                          በዳዊት ፋንታ

በረከት ስምኦን “የሁለት ምርጫዎች ወግ“ የተሰኘ መፅሐፉን በሸራተን አዲስ ሲያስመርቅ ´´አሮጌዋ ኢትዮጵያ እየፈራረሰች በአዲሷ ኢትዮጵያ እየተተካች…………´´ እያለ ተናግሮ ነበር።በእርግጥ በሌላ በኩል ´´ሀገር ማለት ብሄር ብሄረሰቦች እንጂ ወንዝና ተራራው አይደለም፥የግዛት አንድነት ጉዳይ የነፍጠኝነት ጉዳይ ነው´´ እያሉ የወያኔ ርዕሳን ሲናገሩ መስማቱንም ለምደነዋል።
እስኪ በቅርቡ በተዘጋው የወያኔ የ21 ዓመት የመጀመሪያ ምዕራፍ ´´ገነባናት´´ ያሏትን ኢትዮጵያ እና ለትውልድ ያስተላለፉትን ውርስ እንመልከት።

ብርሃንና ሰላም = ጽልመትና ሽብር


“ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት፣ ሳምንታዊውን የፍትሕ ጋዜጣ እንዳይሰራጭ አገደ፤” (www.fetehe.com እና በአዲስጉዳይ መጽሔት፣ ሐምሌ 2004 ዓ.ም)
“ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት፣ ሳምንታዊው የፍኖተ ነፃነት ጋዜጣ እንዳይታተም ከለከለ፡፡” (www.fnotenetsanet.com እና amharic.voanews.com October 02, 2012/ መስከረም 22 ቀን 2005 ዓ.ም)
“ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት፣ የሪፖርተር ጋዜጣን ገጽ ቁጥር ገደበ፡፡” (ሪፖርተር ጋዜጣ፣ ጥቅምት 4 ቀን 2005 ዓ.ም)
ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት በሁሉም ዜናዎች በበጎ ጎኑ አልተነሳም፡፡ “እንዳይሰራጭ አገደ!” “እንዳይታተም ከለከለ!” እና “ቁጥር ገደበ!” የሚሉት ሃረጎች የማተሚያ ቤቱንBerhanena Selam printing press, ethiopia ስምና ክብር የሚያጎድፉ ናቸው፡፡ ይህ ማተሚያ ተቋም፣ የዛሬዎቹ ሹመኞችና ባለሥላጣናቱ አወቁትም – አላወቁትም ትልቅ ራዕይና አላማዎችን አንግቦ የተነሳ ነበር፡፡ እነዚህን ተልዕኮዎቹን ለርካሽ የፖለቲካ ትርፍ ሲባል መስዋዕት ማድረግ ግን ከተጠያቂነትና ከታሪክ-ሕሊና ተወቃሽነት አያድንም፡፡
“ብርሃንና ሰላም የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ማተሚያ ቤት” በመስከረም 3 ቀን 1914 ዓ.ም በአልጋ ወራሽ ተፈሪ መኮንን ተቋቋመ፡፡ ይህ ማተሚያ ቤት በጥቃቅን ፔዳሎች ማለትም በእግር በመርገጥ በሚንቀሳቀሱ የማተሚያ መኪናዎች ሥራውን የጀመረው ስድስት ኪሎ በሚገኘው የዛሬው የቋንቋዎች አካዳሚ ሕንፃ ውስጥ ነበር፡፡ በዚያ ሁናቴ የተጀመረው የብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት  በ1958 ዓ.ም ሠላሳ ሺህ ጋዜጦችን በሰዓት ለማተም የሚችሉ ዘመናዊ የኦፍሴት ማተሚያ መኪናዎች ባለቤት ሆኗል (የዛሬይቱ ኢትዮጵያ፣ ቅዳሜ ኅዳር 18 ቀን 1958 ዓ.ም፤ ገጽ 3 ይመልከቱ)፡፡

ዛሬነገ ሳንል መነሳት የዜግነትግዴታችን ነው!

ለቀድሞው የወያኔ ጠቅላይ ሚኒስትር ለጊዜው ኳሷ በእሳቸው ቁጥጥር ስር እንደሆነች እና የኢትዮጵያ ህዝብን ፍላጎት ማክበር አለበለዚያም የኢትዮጵያ ህዝብ እና ታሪክ ጠላት
Author, writer from norway
አብዶ ኑር የሱፍ (ኖርዌ)
ሆነው የመቀጠል ሁለት ምርጫ እንዳላቸው በኢትዮጵያ ምሁራን በየአቅጣጫው ቢነገራቸውም ፤ በማን አለብኝነት ኳሷን ባለማከፋፈል ችግር ፣ እኔ ብቻ በኳሷ እንደፈለኩ ከምፈልገው ወገን ጋር ልጫወትባት ፣ ስለ ኳሷ አትጠይቁኝ ፣ ወደ ኳሷም አትጠጉ በማለት ቀይ መስመር በማስመር እና እኔ ብቻ አውቃለሁ በማለት በ 80 ሚሊዮን ህዝብ ራእይ እና ተስፋ ላይ እንደቀለዱ እንዲሁም ስልጣን ላይ ሙጭጭ እንዳሉ እና ኳሷን ያለአግባብ በቁጥጥራቸው ስር በማዋል ብሎም የኢትዮጵያ ህዝብ መተንፈስ እንኳን እንዳይችል አድርገው በፍርሃት አስረው በማስቀመጥ በማን አለብኝነት ጢባ ጢቦ እየተጫዎቱ ባሉበት ወቅት ባልትጠበቀ ሁኔታ ጊዜው ደርሶ ወደ ማይመለሱበት አለም አምልጠዋል ፡፡ በስሩት ወንጀል በአለም አቀፍ ፍርድ ቤት ሳይጠየቁ ማምለጣቸው ቢያስቆጭም፡፡

ትውልደ ኢትዮጵያዊያን አሜሪካውያን በ2012 ምርጫ መሳተፍ ይገባቸዋል

ጉዳዩ የምርጫ ብቻ አይደለም እኮ
                          
                                                                        ከፕሮፌሰር ዓለማየሁ ገብረማርያም
                                                                         ትርጉም ከነጻነት 
 

Ethiopian Americans your vote counts vote on November 6 2012
 
ባለፈው ሴብቴምበር ስለ ፕሬዜዳንት ባራክ ኦባማ ድጋሚ መመረጥ ድጋፌን ገልጬ ነበር፡፡ ለታዳሚዎቼ እንዳስነበብኩት በ2008 ምርጫ ተወዳዳሪ ባራክ ኦባማን ደግፌ እንደነበርና ከምርጫው በኋላ ግን በታየው በተለይም ኢትዮጵያንና አፍሪካን በተመለከተ ስለተካሄደው አስተዳደራዊ ፖሊሲ ግን በጣሙን ቅሬታ አድሮብኛል፡፡ እንደትጠቀስኩት:-
 
ፕሬዜዳንት ኦባማ በአፍሪካ ውስጥ ተግባራዊ አደርጋለሁ ያሉትን መልካም አስተዳደርን፤የሰብአዊ መብትን መከበር፤የዴሚክራሲን ተግባራዊነት በተመለከተ ቃላቸውን ጠብቀዋል? በኢትዮጵያ ውስጥ ስላለው የሰብአዊ መብት ገፈፋና ረገጣ ያሉትን አድርገዋል? በጭራሽ! ኢትዮ አሜሪካውያንስ ፕሬዜዳንቱ በአክራ (ጋና) የገቡትን ቃል ስላልጠበቁና የሰነዘሩትን የተስፋ ቃል ባለማክበራቸው ቅር ተሰኝተዋል? አስተዳደራቸውስ በኢትዮጵያ በጉልበት ስልጣን ለያዘው ፈላጭ ቆራጩ ዲክታተራዊ ገዢ ድጋፍ ማድረጋቸውስ ኢትዮ አሜሪካውያንን አሳዝኗል? አዎን በሚገባ እንጂ!
ፕሬዜዳንት ኦባማ ‹‹በአፍሪካ ጠንካራ የሆነ የዴሞክራቲክ ስርአት፤ት የሕግ የበላይ ነት የሚከበርበት፤ለፖለቲካዊ እንቅስቃሴ አድሎ

Will President Obama remember us this time?

by Kirubeal Bekele
We did not vote for Obama enthusiastically as we did in 2008
Well, the US 2012 election is over. Obama has won. Most of us, including me, did not vote for Obama enthusiastically as we did in 2008. What we actually did was vote against Romney.There are two good reasons to vote against Romney. One is racism. This does not need any explanation. It is self explanatory. Look at the red states. And look the percentage differences between Obama and Romney in these red states. That tells you a lot. Any time you want to move or relocate in the States, it is a good idea to avoid these regions.

የሃሪኬን ዐውሎ ነፋሳት መነሻቸው ከኢትዮጵያ መሆኑን የናሳ ሳይንቲስት አረጋግጠዋል

በፍቅር ለይኩን

HARRICANE SANDY GOES FULL
 
የአሜሪካን በተለያዩ ጊዜያት የመቱ አውሎ ንፋሳትና ወጀቦች መነሻቸው ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ተራራማ ቦታዎች መሆናቸውን የናሳ ሳይንቲስቶች ጥናቶች በተለያዩ ጊዜያት ሲያመለክቱ ነበር፡፡ ኦውን ኬሊ የተባሉ የናሳ ተመራማሪ በ2006 ዓ.ም ጥናታቸው፡- A lot of hurricanes start out over the Ethiopian Mountains. Air steadily flowing over those mountains and they cause waves in the air. በማለት የሄሪኬን አውሎዎችና ወጀቦች መነሻ ኢትዮጵያ መሆኗን በጥናታቸው አመልክተዋል፡
 
ሌላኛው የናሳ ሳይንቲስትና ተመራማሪ የሆኑት ስኮት ብራውን እ
ስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ የሄሪኬን መነሻዎች ከባሕሮችና ከውቅያኖሶች ዳርቻዎች ነው ከሚለው በተጨማሪ ለሄሪኬን መከሰት ከምዕራብና ምስራቅ አፍሪካ የሚነሱ ንፋሳትና አውሎዎችም የብዙዎች ሳይንቲስቶችና አጥኚዎች ትኩረትን እየሳቡ መምጣታቸውን በጥናታቸው በአጽንኦት ገልጸዋል፡፡
 
Wall Street Journal የናሳ ሳይንቲስቶችን ጥናት ዋቢ በማድረግ እንዳስነበበው ደግሞ አሜሪካንን የመታው ‹‹ሄሪኬን አርል›› የተባለው አውሎና ወጀብ መነሻው ከኢትዮጵያ እንደነበር በወቅቱ አስነብቦ ነበር፡፡ እንዲሁም እ.ኤ.አ በ2003 ዓ.ም የተከሰተው ‹‹ሄሪኬን ኢሳቤላ›› የሚል መጠሪያን ያገኘችው አውሎና ወጀብም መነሻዋ ከኢትዮጵያ እንደነበር ተገልጾ ነበር፡፡

የሃይለማርያም ቃለመጠይቅ በሻዕቢያ የተዘጋጀ?


Ethiopian Prime Minister Hailemariam Desalegn

 
ከተስፋዬ ገብረአብ

ሰሞኑን ሃይለማርያም ደሳለኝ አንድ አስገራሚ ቃለመጠይቅ ሰጥቶ ነበር። አገር ውስጥ ለሚታተም መፅሄት በሰጠው በዚሁ ቃለመጠይቅ ላይ፣ “ዘላለማዊ ክብር ለመለስ ዜናዊ” በማለቱ ከቤተሰቡ የደረሰበትን ተቃውሞ ገልፆአል። በርግጥም ሃይለማርያም ልጆቹንና ባለቤቱን ሰብስቦ፣ “ተሳስቼያለሁ።” ብሎ ይቅርታ ጠይቆአል። ይህን እንግዲህ ከመፅሄቱ ላይ ያነበብነው ነው። የሃይለማርያም ሴት ልጅም አባቷን በዚህ መልኩ በማረሟ ታዋቂ ሆና ሰንብታለች። በርግጥም ዘላለማዊ ክብር ለአምላክ እንጂ ለሰው የሚሰጥ አልነበረም።
 
በዚሁ ቃለመጠይቅ ሃይለማርያም አንዳንድ አፈንጋጭ የሚመስሉ ቃላት አምልጠውታል። ያነበበው ወረቀት ከእሱ እውቅና ውጭ ተዘጋጅቶ መቅረቡን መግለፁ አነጋጋሪ ነበር። ከጀርባ ያሉትን ዘዋሪ ሾፌሮች የሚጠቁም ነበር። መለስን የሚቃወም ከሚመስሉ የሃይሌ የምላስ ወለምታዎች መካከል፣
“እኛ የአይን ቀለም አንመረምርም” ማለቱ የሚጠቀስ ነው።
መለስ የሚታወቀው የአይናችንን ቀለም በመመርመር ነበር። ሃይለማርያም ይህን የአይን ቀለም ምርመራ ካልተከተለ፣ አንድ ትልቅ ለውጥ ነው። የምላስ ወለምታም ከሆነ እናዋለን።” ብዬ በተስፋ በመጠበቅ ላይ ነበርኩ።
 
ይህ በእንዲህ እንዳለ Ethiopia first እና Aiga forum የተባሉት የወያኔ ድረገፆች ባስነበቡት ዘገባ ዝነኛ ሆኖ የሰነበተው የሃይለማርያም ቃለመጠይቅ፣ “በጠቅላይ ሚኒስትሩ ስም ተቀነባብሮ የተዘጋጀ እንጂ ሃይለማርያም የሰጡት ቃለመጠይቅ አይደለም” ሲሉ አውጀዋል። “ትልቁ ጀበና ተሰነጠቀ” ማለት ይሄኔ ነው። ወያኔ በጉዳዩ ላይ ያወጣው ዘገባ የሚከተለውን ይመስላል።

Who has the mandate in Ethiopia?

Let me add that only a virtuous people are capable of freedom. As nations become corrupt and vicious, they have more need of masters.
Benjamin Franklin
by MeKonnen H. Birru, PhD
Yesterday, over 90 million Americans voted and in Texas time exactly 11:12 PM, the former one term U.S senator from the state of Illinois won his second and last term of the U.S. presidency with 303 electoral votes. Florida’s result still not in but doesn’t matter anymore because the young African American incumbent won six of the seven battle ground states such as Iowa, Colorado, Nevada, and Ohio. “We will pray for him,” said Mr. Romney in his concession speech right before Obama’s hopeful speech. To the rest of us who had been anxiously waiting to see the election result, now the snow is melted, the spring is in, the sun is rising again. Now, we all clearly know who has the mandate to lead this great nation; yes, we have a new democratically elected president. Not just democrats or the 50% who voted for Obama but the entire nation accepts the re-elected Commander in Chief. Yes, the people gave him a mandate to wage war on their behalf, to negotiate on with other nations on their behalf, to tax on their behalf, and to call himself the leader of the free world on their behalf. God bless America. “I know that political campaigns can sometimes seem small, even silly.

Wednesday, October 31, 2012

ESAT Daliy News-Amsterdam Oct. 30 2012 Ethiopia

Ethiopia’s Reeyot: “The Price for My Courage”


by Alemayehu G. Mariam
There are few things more difficult or dangerous than speaking truth to abusers of power. But for Reeyot Alemu, the 31 year-
old young Ethiopian heroine of press freedom, no price is high enough to keep her from being “the voice of the voiceless”. She will speak truth to power even when she is muzzled and gagged and in prison: “I knew that I would pay the price for my courage and I was ready to accept that price,” said Reeyot in her moving handwritten letter covertly taken out of prison.


“Courage is the most important of all the virtues, because without courage you can’t practice any other virtue consistently,” said Maya Angelou, the great African American civil rights advocate and literary figure. Last week, the International Women’s Media Foundation (IWMF) awarded Reeyot Alemu its prestigious “2012 Courage in Journalism Award”. Last May, I wrote a column on Reeyot  (Young Heroine of Ethiopian Press Freedom), expressing my outrage over the “legal” process used to railroad her to prison:
The so-called evidence of “conspiracy” against Reeyot in kangaroo court consisted of intercepted emails and wiretapped telephone conversations she had about peaceful protests and change with other journalists. Reeyot’s articles in Feteh and other publications on the Ethiopian Review website on the activities of opposition groups were also introduced as evidence. Reeyot and Woubshet Taye [editor of Awramba Times] had no access to legal counsel  during their three months in pretrial detention. Both were denied counsel during interrogations. The kangaroo court refused to investigate their allegations of torture,  mistreatment and denial of medical care in detention…

Ethiopian Minister’s Wife Accused of Using Saudi Cash in Unrest



By William Davison (Bloomberg) — Ethiopian authorities charged a minister’s wife with terrorism for using money from the Saudi Arabian Embassy to pay for Islamic protests against the government, defense lawyer Temam Ababulgu said. (Picture: Ethiopia civil service minister Junedin Sado’s wife is implicated in the charge)
Habiba Mohammed, wife of Civil Service Minister Junedin Sado, was among 29 people charged with terrorism offenses in an Ethiopian court yesterday, Temam said yesterday in an interview outside the court in the capital, Addis Ababa.
Nine members of a 17-person committee formed to dispute the government’s control of the Islamic council, which has led the demonstrations, were also among the 29 charged under a 2009 terrorism law the U.S. and United Nations have criticized as too broad. Habiba was charged with belonging to and aiding a terrorist organization, Temam said.
Muslims in Ethiopia, Africa’s second-most populous nation, have been holding protests at mosques for more than a year against government control of an Islamic council, some of which turned violent. The government accuses the group of being led by extremists who want to convert the secular nation into an Islamic state.
A call today to the Saudi Embassy in Addis Ababa was not answered. State Minister of Communications Shimeles Kemal did not immediately answer two calls to his office today.
The defendants will answer the charges at the next hearing, scheduled for Nov. 22, Temam said.