Saturday, July 12, 2014

‹‹ቀዩ መስመር›› የቱ ጋር ነው? ጽዮን ግርማ

ኢትዮጵያ በፓርቲ ላይ የተመሰረተ ፖለቲካ ባህል ውስጥ የገባችው የ1960ዎቹን ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ ተከትሎ ነው፡፡ በዚህም ምክንያት የተለያዩ ርዮተ ዓለሞች ተፋጭተው ዴሞክራሲያዊ ሥርዐት ይመሰረትባታል በሚል ተስፋ ቢጣልም የድርጅቶቹ የኋላ ታሪክ እንደሚያስረዳው ለሀገርና ለሕዝብ የሚጠቅም ለውጥ ከማምጣት ይልቅ እርስ በእርስ የመጨራረስ ባህል እንደነበራቸው ነው፡፡ ከበርካታ ንፁሃን ዜጎች ደም መፍሰስና እልቂት በኋላ ህወሓት ኢሕአዴግን መሥርቶ ወደ ሥልጣን ሲመጣም ከሻዕቢያ በስተቀር ሌሎቹ ድርጅቶች እስከ አመራሮቻቸው ደብዛቸው ጠፍቶ ነበር።ኢህአዲግ የሥልጣን ወንበሩን ከጨበጠ በኋላ በሽግግር መንግሥት ምስረታ ፓርቲዎች እንዲሳተፉ ይፋዊ ጥሪ በማስተላለፍ በፓርላማ መቀመጫ እንዲያገኙ በማድረግ ዴሞክራሲያዊ ሥርዐት የተመሰረተ ለማስመሰል ጥረት ቢያደርግም በተለያየ ምክንያት አባሮ መልሶ ለመበታተን ጊዜ አልወሰደበትም ነበር ፡፡

አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን በተመለከተ ከኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር/ኢሕአግ/የተሰጠ መግለጫ


 የማፈኛ መዋቅሩን መሰረት በማድረግ በርካቶች ጀግኖች ኢትዮጵያዊያን እጅግ በከፋና በሚዘገንን ሁኔታ በማጥፋት እኩይ ተግባሩ የሚታወቀው አረመኔው የወያኔ ስርዓት በአገራችን የተንሰራፋውን መጠነ-ሰፊ ተግዳሮት ከመሰረቱ ለመንቀል በሚደረገው ትግል ብርቱ ጥረትና እንቅስቃሴ ሲያደርጉ በነበሩት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ከየመን መንግስት ጋር በማበር የአንድን ሰው ከአገር አገር የመንቀሳቀስ መብት በመጣስ የየመን መንግስት ለወያኔው ማስረከቡ አጥብቀን የምናወግዘውና የምንቃወመው ሲሆን ድርጅታችን የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር በአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ላይ በደረሰው አፈና መሰረት በማድረግ ማንኛውንም አይነት እርምጃ የምንወስድ መሆናችንን አበክረን እናስታውቅለን።

Friday, July 11, 2014

ትግል!!! ማንን? ለምን? ለማን? በማን? በምን? መቸና የት?

ትግል!!! ማንን? ለምን? ለማን? በማን? በምን? መቸና የት?

(ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው)
struggle


ሀገራችን እድሜ ጠገብ፣ እድሜ እረጅም መሆኗን እናውቃለን፡፡ ከኖሕ ዘመን (ከጥፋት ውኃ) በኋላ ያለውን ብቻ እንኳን ብንይዝና ከመጀመሪያው ንጉሥ ከሰብታህ ጀምረን ብንቆጥር ከ4500 ዓመት በላይ ዕድሜ ያለው የመንግሥት መልክ የያዘ የአሥተዳደር ታሪክ ያላት ሀገር ናት፡፡ ይህች ሀገር ከዚህ ረጅም ታሪኳ ጋር እንደ ፀሐይ የሚያበራና አድማስ ተሻግሮ የሚሞቅ ብርቅዬ የነጻነት ታሪክ አላት፡፡ ሀገራችን ከ3 ሺህ ዓመታት በፊት ጀምሮ ይሄንን ዘውዷም ለመንጠቅ የሞከሩ እጅግ ከባባድ ፈተናዎችን አሳልፋለች፡፡ ፈተናው ያንን ያህል የከበደ ቢሆንም ያ ሕዝብ ከጠላቶቹ ከፈታኞቹ ከተገዳዳሪዎቹ ሁለንተናዊ አቅም የላቀ ጥንካሬ ብስለት ንቃት ወዘተ ስለነበረው ዘውዱን ሳያስነጥቅ ጠብቆ ለመቆየት ችሏል፡፡ ነገር ግን በመራር ጽናት ነጻነቱን ጠብቆ መቆየት ይቻል እንጅ ከጥንት ጀምሮ የነበረበት ፈተና ድምር ውጤት ይሁን ወይም ምድሪቱ አርጅታ አይታወቅም ከጥቂት ዐሥርት ዓመታት ወዲህ ያለውን ትውልድ ስናይ ከትውልዱ የሚበዛው ምርኮኛና ምንደኛ የሆነ ትውልድ አፍርታ ቁጭ ብላለች፡፡

ፅናት

               ፅናት
                                                   
                                                                            ከምናሴ መስፍን
                                                                            ከኖርዌ ኦስሎ 

ይህን ዕርዕስ ስመርጥ ስለ ፅናት ትንታኔ ለመስጠት ሣይሆን ወይም ለፅናት ያለኝን አመለካከት ለመግለፅና ትምህርታዊ ዘገባ ለማቅረብ አይደለም ።

ይልቁንም ፅናት ምን እንደሆነ ከፅናት ባለቤቶች ዘወትር ፅናት የሚሰብኩ ኢትዮጵያዊነታቸው አይሎ ሕዝባዊ ወገንተኝነታቸው ጉልቶ እድሚያቸው ሙሉ በውስጣቸው የፍም እሣት
የሆነው ሃገራዊ ፍቅር በማንኛውም አይነት የግል ጥቅም ሳይሸነገሉና ሳይደለሉ ክብር ሕይወታቸው ለህዝብ ቤዛ ያደረጉ በለስ የቀና በጣርነት አውድማ ላይ ከፀረ ሕዝብና ፀረ ዲምክራሲ ከህዝብ ጠላቶች ጋር ሳንጃ ለሳንጃ ተሞሾላልቆ አኩሪ መሠዋትነት ሲከፍል አንዳንዱ ደግሞ ከጣርነት ሜዳ ውጭ ሠላም ባለበት አጋርና መንግስት ባለበት የበአድ አገር
ላይ በጣላት እጅ ይወድቅና ፅናት ምን ንደሆነ በአይበገሬነት የጠላት ዱላ ግልምጨና ወከባ ሣይባግረው ወይ ፍንክች ሣይል ዛሬም ለህዝብ መቆሙን በጠላት ሚዲያ ሳይፈራ በጠንካራ መንፈስና አንደበት ለአመነበት አላማ ለፍትህና ለኩልነት ለሠላምና ለብልፅግና ፀንቶ ሰሞኑ ስላየሁት አንዳርጋቸውን ፅጌ ትንሸ ለማለት ብዩ ነው ።

ዓረና-መድረክ በራያ አዘቦ “ዘመቻ አብረሃ ደስታ” በሚል ሕዝባዊ ስብሰባ ጠራ


  • 188
     
    Share
(አብርሃ ደስታ ከመቀሌ)
(አብርሃ ደስታ ከመቀሌ)
ዓረና-መድረክ እሁድ  ሐምሌ 06 2006 ዓ/ም በራያ ዓዘቦ ወረዳ ሞኾኒ ከተማ “ዘመቻ ኣብረሃ ደስታ” የሚል መፎክር ያለበት ህዝባዊ ስብሰባ ያካሂዳል።
ዓረና-መድረክ ፖሊሲው፣ ስትራተጂውና ኣማራጭ ሃሳቡ ከራያ ዓዘቦና ኣከባቢው ህዝብ ለመወያየትና ለማስተዋወቅ ህዝባዊ ስብሰባ ጠርተዋል።
ዓረና-መድረክ የሃገራችን የፍትህ፣ ዲሞክራሲ፣ መልካም ኣስተዳደር፣ ሁላቀፍ ልማት፣ የሚድያ ነፃነት፣ ወዘተ ተግዳረቶች በማቅረብ ለነዚህ ችግሮች መፍትሄ ኣማራጭ ሃሳቦች በማቅረብ ወደፊት ሃገራችን የምትመራበት ዲሞክራሲያዊ ስርዓት ምን መምሰል እንዳለበት፣ ሰለማዊ የስልጣን ሽግግር እውን የሚሆንበት ኣግባብ፣ ባለፈው 17 የትጥቅ ትግል የተከፈለ መስዋእትነትና በኣሁኑ ሰዓት የተገኘው ለውጥ ምን እንደሚመስል ከራያ ህዝብ እንወያያለን።
ጀግናው የራያ ህዝብ የጀንነትና የጀግና ኣድናቂ ነው። የዚህ ህዝባዊ ስብሰባ መጠርያም የኣዲሱ ትውልድ ጀግና የሆነው “ኣብራሃ ደስታ” እንዲሰየም ተደርጓል። ስለዚህ “ዘመቻ ኣብራሃ ደስታ” ከራያ ህዝብ ጋር ለዲሞክራሲያዊ ለውጥ የምንወያይበትና ኣብረን የምንታገልበት መድረክ ይሆናል።
የዓረና ስራ ኣስፈፃሚ ኣባል የሆነው ኣብራሃ ደስታ በኣሁኑ ሰዓት በኣዲስ ኣበባ ማእከላዊ በመባል የሚታወቀው ማረሚያ ቤት እንደሚገኝ ምንጮች ገልፀዋል።

Thursday, July 10, 2014

መንግስታዊ ሽብርተኝነትን የሚሸከም ትከሻ አይኖረንም!!!ከሰማያዊ ፓርቲ የተሰጠ መግለጫ
ሀምሌ 3/2006ዓ/ም

የህወሓት/ኢህአዲግ አገዛዝ በኢትዮጵያ ስልጣን ላይ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ ዜጎችን በማፈንና በማሰቃየት ብሎም በመግደል የአፈና አገዛዙን ለረጅም ጊዜ ሲያራምድ መቆየቱ ዓለም የሚያውቀው ሀቅ ነው፡፡ በተለይም ባለፉት 10 ዓመታት የህዝብን ሰላማዊ እንቅስቃሴ ለማፈን እስራትና ግድያውን ህጋዊ ለማስመሰል የተለያዩ አፋኝ አዋጆችን አውጥቷል፡፡ እነዚህን አዋጆችንም ተገን አድርጎ በሰላማዊ መንገድ የሚታገሉ የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎችንና አባለትን፣ ጋዜጠኞችንና ጦማርያንን፣ እንዲሁም የእምነት ተቋማት መሪዎችን እና በአገዛዙ ላይ ጥያቄ የሚያነሱ ዜጎችን ማሰሩን፣ ማሰቃየቱንና ግድያውን ተያይዞታል፡፡ በህገ መንግስቱ የተካተቱ የሰብዓዊ መብቶችንና ዓለም አቀፍ ስምምነቶችን በሙሉ የሚጥሰውና የአምባገነንነት ስልጣኑን ለማራዘም ሲል ያፀደቀው የፀረ-ሽብር አዋጅ ከፀደቀበት እለት አንስቶ ኢህአዴግ ለስልጣኔ ያሰጉኛል የሚላቸውን ፍፁም ሰላማዊ ታጋዮችንና ህገ መንግስታዊ መብታቸውን ተጠቅመው በድፍረት የፃፉ ጋዜጠኞችን ብሎም የእምነት ነፃነታችን ይከበር ብለው የጠየቁ የሀይማኖት መሪዎችን በጠራራ ፀሃይ ያለምንም ወንጀል በዚሁ ህገ ወጥ አዋጅ ‹‹የፀረ ሽብር ግብረ ሀይል›› በሚባል ማንነቱ በማይታወቅ የጨለማ ቡድን ወደ እስር ቤት እያጋዘ ይገኛል፡፡

ያማል ግን ይህን እመም ለመቻል ቁርጠኝነት ይጠይቃል፡፡


10494588_750671571658261_8784450188684809422_nhabtamu ayalewየፓርላማ አባልና የአንድነት ከፍተኛ አመራር አባል አቶ ግርማ ሰይፉ የኢሕአዴግ መንግስት በሰላም የሚታገሉ ወጣት ፖለቲከኞችን የማሰሩን ጉዳይ እብድነት ብለዉታል።

«እነዚህ ሰዎች አብደው መሆን ይኖርበታል፡፡ ሀብታሙ አያሌውን ፖሊሶች ይዘውት እንደሄዱ ሰማው፡፡ ስልኩ ይጠራል ግን አይመልስም፡፡ የእነርሱን ሃሳብ የሚቃወም ሁሉ አሸባሪ እየመሰላቸው በሽብር እራሳቸውን እያናወዛቸው ያለ ይመሰለኛል፡፡ ሀብታሙን ሊያስሩት ይችላሉ በህዝብ ውስጥ ያለውን የነፃነት መንፈስ ግን ማስረ አይቻላቸውም፡፡ እልፍ አህላፍ የነፃነት ሰዎች ይፈጠራሉ፡፡ ለነገሩ የሚታሰሩ ንፁሃን ታሳሪዎች ሳይሆን አሳሪዎ በከፍተኛ የህሊና ስቃይ ውስጥ መሆናቸውን መረዳት አሰቸጋሪ አይደለም፡፡» ሲሉ ነበር አቶ ግርማ በፌስ ቡክ አስተያየታቸውን የሰጡት።

«የዚህ ልጅ ነገር ሳያበሳጫቸው አይቀርም፡፡ ሰለማዊ ሰልፍ ላይ በባትሪ አንደሚሰራ ሳያርፍ ያጋልጣቸዋል፡፡ በየሳምንቱ ገበናቸውን በመፅኄት በጋዜጣ ያወጣል፡፡ በዓመት መጨረሻ ደግሞ ትምህርት ተምሮ በክብር በማዕረግ ይመረቃል፡፡ ኢዚህም እዚያም ያገኙታል ሁሉም ጋ ሲያወግዛቸው፤ በቃችሁ ሲላቸው ይሰማሉ፡፡ በቃቸው የሚላቸው ደግሞ እንደበቃቸው ስራቸው ሆኖ ያያቸው እርሱ መሆኑ ያበሳጫቸዋል፡፡